arrow-left-dark
Back

ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በኢትዮጵያ ለሚገኙ የዓይነ ስውራን ተማሪዎች ሁሉን አቀፍ የትምህርት እድልን ለማስፋፋት የሚያስችል የ60 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ታሪካዊ የበጎ አድራጎት ፕሮጀክት ይፋ አደረገች

Dot
14 ፌብሩዋሪ 2025
|
  አቡዳቢ

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት በልዑል ሼክ ሙሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያ መመሪያ መሰረት፣ ኤምሬቶች በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የዓይነ ስውራን ተማሪዎችን የትምህርት ፍላጎት ለማደገፍ የሚያስችሉ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል የ60 ሚሊዮን USD (220 ሚሊዮን AED) አዲስ የድጋፍ ፕሮጀክት በኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያ ፋውንዴሽን በኩል ይፋ አድርጋለች።

 

ከኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር በመተባበር፣ በኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያ ፋውንዴሽን የሚደረገው የ60 ሚሊዮን USD (220 ሚሊዮን AED) ኢንቨስትመንት አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እና ሁሉን አቀፍ የትምህርት ፕሮግራሞችን ለመደገፍ ይውላል።

 

 ይህ በጎ አድራጎት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሁሉንም ያካተተ ማህበረሰብን ለመገንባት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ ለሚገኙ የዓይነ ስውራን ተማሪዎች የትምህርት እድልን ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት በስፋት ለመደገፍ ያላትን ቀጣይነት ያለው አቋም ያረጋግጣል።

 

ከኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር በመተባበር ይህንን የበጎ አድራጎት ስራ የሚመራው የ'ኤርት ዛይድ ፊላንትሮፒስ' አባል የሆነው የኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያ ፋውንዴሽን ነው። ይህም ፕሮጀክት በግንቦት 2024 አዲስ አበባ ውስጥ የተመረቀውን የእመቤታችን ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት ስኬት መነሻ ያደረገ ነው። ስምምነቱ የተፈረመው በኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያ ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር በክቡር አቶ ሙሐመድ ሐጂ አል-ኮሪ ሲሆን፣ በስነ-ስርዓቱም ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዛይድ ፊላንትሮፒስ የበላይ ጠባቂ ክቡር ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን እና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመጀመሪያዋ እመቤት ክብርት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

 

በኢትዮጵያ ውስጥ 332,000 የሚያህሉት ሙሉ በሙሉ ዓይነ ስውራን የሆኑትን ጨምሮ ወደ 1.2 ሚሊዮን የሚጠጉ የዓይን ሕመም ያለባቸው ግለሰቦች እንዳሉ ይታመናል። በመሆኑም ይህ በጎ አድራጎት የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች ውስን ወደሆኑበት የገጠር አካባቢዎች በመድረስ አጣዳፊ የሆነን ሰብዓዊ ፍላጎት በቀጥታ ይፈታል።

 

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ መከላከል የሚቻለውና አነስተኛ አገልግሎት የሚያገኙ ማህበረሰቦችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠቃው የትራኮማ በሽታ በስፋት ከሚታይባቸው አገራት አንዷ ናት። በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ እነዚህ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ዘመናዊ አጋዥ ቴክኖሎጂዎችን፣ ልዩ የትምህርት ካሪኩለሞችን እና ተስማሚ የሙያ ስልጠና ፕሮግራሞችን በማቀናጀት የዓይነ ስውራን ተማሪዎችን ለከፍተኛ ትምህርት እና ለስራ ዓለም የሚያስፈልጋቸውን ክህሎት የሚያስታጥቁ የምርጥ ብቃት ማዕከላት ሆነው የሚያገለግሉ ይሆናል።

 

የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የልማትና የጀግኖች አርበኞች ጉዳይ ምክትል ሊቀመንበር፣ የዓለም አቀፍ ሰብዓዊና የበጎ አድራጎት ምክር ቤት ሊቀመንበር እንዲሁም የ'ኤርት ዛይድ ፊላንትሮፒስ' የቦርድ ሰብሳቢ ልዑል ሼክ ዚያብ ቢን ሙሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ሲናገሩ፦ «ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አካል ጉዳተኞችን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች። ከነዚህም መካከል ዋነኛው በኢትዮጵያ የሚገኝ የዓይነ ስውራን ተማሪዎች ልዩ ፍላጎታቸውን የሚያሟሉ፣ የሚያነሳሱና ሁሉንም ያካተቱ የትምህርት አካባቢዎችን ማግኘት እንዲችሉ ማረጋገጥ ሲሆን፣ ይህም ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል። ይህ በጎ አድራጎት ማንኛውም ሰው የጋጠመው ፈተና ምንም ይሁን ምን፣ ሁሉንም ባካተተና እኩል በሆነ የዓለም ማህበረሰብ ውስጥ አድጎ ውጤታማ መሆን እንደሚችል ለማረጋገጥ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት ያሳያል» ብለዋል።

 

የካቢኔ አባልና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመንግስት ሚኒስትር ክቡር ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ሲናገሩ፦ «ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዘላቂ ልማት እና ስትራቴጂካዊ ትብብር ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ዋና ዋና ሃላፊዎች መሆናቸውን ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ትረዳለች። ይህ በጎ አድራጎት ማህበረሰቦችን ለማሳደግ፣ ኢኮኖሚያዊ እድሎችን ለመፍጠር እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ተደረሽ ለማድረግ ያለንን ያልወለወለ ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ነው። አጋርነታችን የአፍሪካ ሀገራት ትምህርት ላይ በመዋለ ንዋይ በማፍሰስ የወደፊት ብልፅግናን ለማረጋገጥ፣ ወጣቶች ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙና ዘላቂ እድገትን እንዲመሩ ለማስቻል ያላቸውን ራዕይ ያጠናክራል» ብለዋል።

 

ኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመጀመሪያዋ እመቤት ክብርት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው አክለው ሲናገሩ፦ «ማንኛውም ዜጋ ከአካላዊ አቅሙ ውጭ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኝ ለማድረግ የምናደርገውን ጥረት ለሚደግፈውና ቀጣይነት ላለው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አጋርነት ምስጋናችን የላቀ ነው። የጋራ ቁርጠኝነታችን እያንዳንዱ ተማሪ የስኬት እድል የሚያገኝበትን እና ሁሉንም ያካተተ ማህበረሰብ ለመፍጠር ይረዳል» ብለዋል።"

 

የኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያ ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሙሐመድ ሃጂ አል-ኮሪ ሲናገሩ፦ «ትምህርት መሰረታዊ መብት ነው፤ እያንዳንዱ ልጅም ልዩ ፍላጎቱን በሚደግፍ አካባቢ ውስጥ የመማር እድል ይገባዋል።

 

የትምህርት ስርዓቶችን በማጠናከር፣ ሁሉንም ያካተተ እና እኩልነት ያለው የወደፊት ጊዜ መሰረት እያጣልን እንገኛለን። ይህ በጎ አድራጎት ዘላቂ ተጽእኖ ለማምጣት የዓለም አቀፍ አጋርነትን ህያው ሀይል የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ትምህርት ለወደፊት ትውልዶች የእድልና የብቃት ምንጭ ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል» ብለዋል።

 

ዛሬ ይፋ ከተደረጉት አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ጋር አብሮ የሚሰራው የ'እመቤታችን ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት'፣ በመላው ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የትምህርት እድልን ለማስፋፋት የሚያስችል ትስስር (ኔትወርክ) ይፈጥራል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያን የትምህርት መሰረተ ልማት ለማጠናከር ያላት ቁርጠኝነት፣ ማንኛውም ዓይነ ስውር የሆነ ልጅ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዳራው ምንም ይሁን ምን፣ ለማህበረሰቡ አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚያስችለውንና አቅሙን የሚያጎለብት የድጋፍ መማሪያ አካባቢ አግኝቶ እንዲያድግ ያረጋግጣል።"

 

በፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) መምህር የሆኑት ፍቅሩ በጆ ሲናገሩ፦ «የተማሪዎቻችን ፈተናዎችን የማሸነፍ፣ በራስ መተማመናቸውን የማሳደግ እና ግባቸውን የማሳካት አስደናቂ የመቋቋም አቅምና ቁርጠኝነት በእጅጉ ያነሳሳኛል። የእነሱ እድገት የትምህርት ለውጥ አምጪነት ሀይል ዘወትር ማስታወሻችን ነው። ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተደረገው ለጋስ ድጋፍ ምስጋና ይግባውና ተቋማችንን አጠናክረናል፣ ለመምህሮቻችን ልዩ ስልጠና ሰጥተናል፣ እንዲሁም የተማሪዎቻችንን የመማር ልምድ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሻሽሉ አጋዥ ቴክኖሎጂዎችን አስተዋውቀናል» ብለዋል።"

 

አክለውም ይህ ድጋፍ ተማሪዎችን ለስኬት ያዘጋጀ ከመሆኑም በላይ የሚሰጡትን የትምህርት ጥራት ከፍ ማድረጉን ገልጸዋል። «በተጨማሪም የተሻሉ እድሎችንና ብሩህ ተስፋን እንደሚያገኙ ማወቃቸው በተማሪዎቻችንና በቤተሰቦቻቸው ዘንድ የተስፋና የበጎ እይታ ስሜትን ፈጥሯል» ብለዋል።"

 

ኤርት ዛይድ ፊላንትሮፒስ (Erth Zayed Philanthropies) በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታዩ እድገቶችን ለማፋጠን እና አነስተኛ አገልግሎት የሚያገኙ ማህበረሰቦችን ለማበቃት የሚሰሩ ልዩ ልዩ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን ይደግፋል።"

Also-Available